ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው ቡና ውስጥ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው ለአውሮፓ ገበያ ይውላል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከምትልከው ቡና ውስጥ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው ለአውሮፓ ገበያ እንደሚውል የአውሮፓ ቡና ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ፌዴሬሽኑ በቅርቡ ባወጣው አዲስ ሪፖርት የኢትዮጵያ ቡና በአውሮፓ ገበያ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ተፈላጊነት እያገኘ መምጣቱን እና የገበያውን 5 በመቶ ድርሻ መያዙንም ጠቅሷል፡፡
አውሮፓ የአለምን 28 በመቶ የቡና ፍጆታ በመሸፈን አሁንም ድረስ የአለማችን ቁጥር አንድ የቡና ገበያ ሆና መቀጠሏን ያነሳው ሪፖርቱ ዘርፉ በህብረቱ 27 ሀገራት ውስጥ በመቶ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅስም ነው የጠቀሰው፡፡
እንዲሁም የአውሮፓ ህብረትን የቡና ገቢ ምርት 34 በመቶ የምታስገባው ጀርመን ስትሆን ጣልያን፣ ስፔንና ፈረንሳይ ከፍተኛ ቡና ሸማች ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደሚገኙበትም ተጠቁሟል፡፡
በዓለማችን ላይ የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት ጀርመን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቤልጂየም፣ ቻይና፣ አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ጃፓን ቀዳሚ ሀገራት ናቸው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
