EthiopiaNews

እየተዛመተ የመጣው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ( MPox )

አፍሪካ ሲዲሲ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የአህጉሪቱ የጤና ስጋት ሆኗል ሲል አስጠንቅቋል ።

የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከያ ማእከል የበሽታው የስርጭት ፍጥነት በእጅጉ አስጊ ነው በዚህ ከቀጠለ ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል ብሏል።

ሲዲሲ ያወጣው ማስጠንቀቂያ ደወል ተከትሎ  አገራት ያላቸውን አቅም አስተባብረው የበሽታው አስከፊነት የሚያመጣውን ስጋት ከወዲሁ ለመቆጣጠር እና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ይኖርባቸዋል ብሏል።

ድርጅቱ እንዳለው ከፈረንጆቹ ጥር 2022 ጀምሮ በቀጠናው 38 ሺህ 465 ሰዎች በበሽታው ሲጠቁ ከ1 ሺህ 456 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአገራችን ከዚህ ጋር በተያያዘ እስካሁን የተያዘ ሰው የለም ሲል የጤና ሚኒስቴር እየተናገረ ነው።  ለሁሉም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።