EthiopiaNews

ዓባይ ባንክ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና በይፋ ተመዝግቧል

ዓባይ ባንክ አክሲዮን ማህበር በኢትዮጵያ የሰነድ መዋለ ንዋይ ገበያ ዋና የግብይት መድረክ ላይ በይፋ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ንዋዮች ገበያ አስታውቋል፡፡

የምዝገባ ሂደቱን የሚያበስረው የደወል መደወል ስነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ባንኩ በገበያው መመዝገቡ ለግልጽነት፣ ለጠንካራ ተቋማዊ አስተዳደርና ለባለአክሲዮኖች ዘላቂ እሴት ፈጠራ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል ባንኩ በዋናው ገበያ ላይ መመዝገቡ ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥነ ምህዳር ለውጥና ዕድገት ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው ኩባንያው በገበያው  ውስጥ እንደመመዝገቡ በቀጣይ ዕድገትና ስኬት እንዲያስመዘግብ ከጎኑ እንቆማለን ብለዋል፡፡

ይህ ምዝገባ ኩባንያዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ በገበያው ላይ ያለውን እምነት የሚያጠናክር እና በኢኮኖሚው ውስጥ የረጅም ጊዜ ካፒታል እንዲንቀሳቀስ የሚያግዝ በግልጽና ቀልጣፋ  ሥርዓት የሚመራ የካፒታል ገበያ ለመገንባት ያለመውን የገበያውን ራዕይ የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

ዓባይ ባንክ በበኩሉ በሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያው ለመሳተፍ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ አደረጃጀት መፍጠር፣ ሰራተኞቹን ማሰልጠን የመሳሰሉ ዝግጅቶችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁሞ ይፋዊ የአክሲዮን ግብይት ለማድረግ የሚያስችለውን እውቅና ማግኘቱን ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv