የሉሲ ሙዚየም በሰመራ
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በ329 ሚሊዮን ብር በጀት የሉሲ ሙዚየም ሊገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው ሙዚየሙ የአፋር ክልልን ባህልና የሁሉንም አርክዮሎጂ ቅሪት ወይም ስብስብ ማዕከልን ያቀፈና በአከባቢው ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ አካላት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር እንዲሁም ክልሉን የበለጠ ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ሀገር የቱሪዝምን ዘርፍ ለማነቃቃት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው በቀጣይም ሀገርን የሚመጥን ትልቅ ብሔራዊ ሙዚየም ለመገንባት የቅድመ ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አፋር ክልል ኢትዮጵያን በዓለም ያስተዋወቁ እንደ አርዲ፣ ሰላምና ሌሎች በርካታ ቅሪተ አካላት መገኛ እንደ መሆኗ መጠን የሉሲ ሙዚየም በክልሉ መገንባቱ ለአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ ለሀገር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ተብሏል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
