EthiopiaNews

የመኪና አደጋ

🔸የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዛሬ በመዲናዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተባበሩት አደባባይ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን እና በ3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን አስታወቀ።

🔸የትራፊክ አደጋ የተከሰተው በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 1 ሰዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው የተባበሩት አደባባይ ነው።

🔸በአደጋውም የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

🔸አደጋው የአልያንስ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከአቤም ወደ የተባበሩት አቅጣጫ ቁልቁለቱን በመጓዝ ላይ ሳለ ከአያት ወደ ሲኤምሲ አቅጣጫ እየተጓዙ የነበሩ ቪትዝ እና ፒካፕ ተሽከርካሪዎችን በመግጨቱ እንደተከሰተ ተገልጿል።

🔸በአደጋውም የፒካፕ መኪናው አሽከርካሪ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በውስጡ ተሳፍረው የነበሩ ሁለት የ7ኛ እና የ5ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች እንዲሁም የቪትስ መኪናው አሽከርካሪ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተነግሯል።

👉መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews