የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ40 ቀናቱ የአሜሪካ-እስራኤል-ኢራን ጦርነት ቀውስ ሳቢያ 32 ሚሊዮን ሰዎች ድህነት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ አስታወቀ።
የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ባወጣው አዲስ ሪፖርት በጦርነቱ ምክንያት ያጋጠመው የነዳጅ እና የንግድ መስተጓጎል 162 ሀገራትን ለአደጋ ማጋለጡን ጠቅሷል።
ፕሮግራሙ ምንም እንኳን አሜሪካ እና ኢራን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢፈራረሙም በጦርነቱ ሳቢያ 32 ሚሊዮን ሰዎች ድህነት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።
ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ እና ነዳጅን ጨምሮ ሸቀጦችን ከውጭ የሚያስገቡ ሀገራት በእጅጉ ተጎጂ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡
ዘገባው የአር ቲ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
