EthiopiaNews

የምርጫው መጠናቀቅ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

የምርጫ ኮማንድ ፖስቱ በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ መሆኑን ገልፆ ትናንት ግንቦት 24 በተጠናቀቀው የድምፅ መስጠት ሂደት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙን አስታውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ የድህረ ምርጫ ሂደቱ በተመሳሳይ በሰላም እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል። መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተገኘ ነው

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv