የምርጫው ድምፅ አሰጣጥ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት በተጠናቀቀው የድምፅ አሰጣጥ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰአት ድረስ በነበረ መረጃ 40 ሚሊየን የሚጠጉ መራጮች ድምፅ መስጠታቸውን አስታወቀ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሃይሉ ይሄን ያሉት የ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በይፋ መጠናቀቁን በተመለከት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ሰብሳቢዋ የቦርዱ የምርጫ ዴስክ ባለሙያዎች በስልክ እና በመልእክት በሰበሰቡት መረጃ 40 ሚሊየን የሚጠጉ መራጮች ድምፅ መስጠታቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።
ሰብሳቢዋ ቆጠራ በሚደረግባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የፓርቲ ወኪሎች መኖራቸውን ቦርዱ እያጣራ መሆኑን ገልፀው በዚሁ የቆጠራ ሂደት ላይ ታዛቢዎች እና የፓርቲ ወኪሎች ባሉበት እንዲደረግ እያበረታታን ነው ብለዋል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
