የሞባይል ስልክ ስርቆት
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የባልትና ዕቃ የሚገዙ በመምሰል ሞባይል ስልክ ስርቆት ሲፈፅሙ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ መቅደስ ተስፋዬ፣ ያሬድ ሙሉጌታ እና ኤፍሬም አብርሀሌ የተባሉ መሆናቸውን ገልፆ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አርባ ዘጠኝ ሎሚ ከለር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ነው ብሏል።
ተጠርጣሪዎቹ ቪትስ ተሽከርካሪ በመጠቀም በክፍለ ከተማው የተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ባልትና መሸጫ ቤቶችና ብቻቸውን የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን በመከታተል ሞባይል ስልኮችን በመቀማትና በመስረቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ እንደለመዱት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በክፍለ ከተማው ወረዳ 5 አርባ ዘጠኝ ሎሚ ከለር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ከሚገኝ ባልትና መሸጫ ሱቅ በመሄድ የዋጋ ግምቱ 45000 ሺህ ብር የሚሆን ሞባይል ስልክ ሰርቀው በተሽከርካሪያቸው ሊያመልጡ ሲሉ በአካባቢው በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ ባደረገው ፍተሻ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 4 ሞባይል ስልኮች የተገኙ ሲሆን በግለሰቦቹ ወንጀል የተፈጸመባቸው ዜጎች ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ንብረታቸውን መምረጥና መረጃ መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
