የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች
🔸የትምህርት ሚኒስቴር በመጪው የ2019 አ.ም የትምህርት ዘመን በራስ ገዝነት ሽግግር መመሪያ መሰረት 60 በመቶና ከዚያም በላይ የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ አስታወቀ።
🔸ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ወደ ራሰ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሽግግር የሚገቡ ዩኒቨርስቲዎች የዝግጅት ግምገማ መድረክ ላይ ነው።
🔸ሚኒስቴሩ በመጪው የትምህርት ዘመን ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጀው መሥፈርት መሠረት የራሳቸውን ግለ ግምገማ በማድረግ ሪፖርት ማቅረባቸውን ገልጿል።
🔸ተቋማቱ ያቀረቡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግም የትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅቶቻቸውን በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎች በተውጣጡ ፕሮፌሰሮችና ሌሎች ምሁራን ገለልተኛ ግምገማ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ እየተገባ እንደሆነ ተገልጿል።
🔸ግምገማው ሲጠናቀቅም ግምገማው ከተካሄደባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 60 በመቶና በላይ የግምገማ ውጤት የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ሽግግር ሂደቱ የሚገቡ እንደሆነ ተመልክቷል።
🔸በዚህም ዩኒቨርስቲዎቹ ያሉበትን ሁኔታ የሚመለከት የግምገማ ቡድን ወደ ተቋማቱ የሚሰማራ ሲሆን የግምገማው ስራውም ከዛሬ ጀምሮ እንደሚጀመር በመድረኩ ተገልጿል።
🔸ከመጪው 2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ራስ ገዝነት ሽግግር እንዲያደርጉ ከሚጠበቁ ዩኒቨርስቲዎች መካከልም መቀሌ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር ፣ጅማ ፣ ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ ፣ ሐረማያ እንዲሁም የአዲስ አበባና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች እንደሚገኙበት ተነግሯል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
