EthiopiaNews

የስራ እድል በካናዳ

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ዜጎች ለስራ ወደ ውጪ ሀገራት እንልካለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሯ ማሳሰቢያውን የሰጡት ዜጎችን አሰልጥኖና አብቅቶ ወደ ካናዳ ሀገር ለስራ ለመላክ መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው ፊውቸር ፊል ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ተቋም ጋር ስምምነት ባደረጉበት መርሀ ግብር ላይ ነው፡፡

ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለቱም ሀገራት መንግስታት እውቅና ኖሮት የተደረገ ስምምነት መሆኑ የተነገረ ሲሆን በኢትዮጵያና ካናዳ በኩል ድልድይ በመሆን አቅምና ብቃት ያላቸው ዜጎችን ከስራ እድል ጋር የሚያገናኝ መሆኑም ተነግሯል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews