የቀጠለው የአሜሪካና የኢራን ግጭት
አሜሪካና ኢራን ለሁለተኛ ቀን መካከለኛው ምስራቅን ያካለለ ጥቃት መሰነዛዘራቸው ተሰምቷል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት ዳግም ግጭት ውስጥ መግባት ደግሞ በቋፍ ላይ ያለውን የተኩስ አቁም ስምምነት አደጋ ላይ ይጥለዋል የሚል ስጋትን አጭሯል ቢባልም የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ጥቃቱን የፈጸምኩት ራስን ለመከላከል ነው ብሏል፡፡
አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን በሚገኙ የራዳርና የአየር መቃወሚያ ስርዓቶች ላይ ጥቃት ማድረሷ ሲነገር ጥቃቱ የተፈጸመውም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ በመውሰዷ ከባድ ምት ያርፍባታል ካሉ በኋላ ነበር፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ባወጣው መግለጫ ቴህራን በባህሬን፣ ኩዌትና ዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ በፈጸመችው ጥቅት የጦር ጄቶችና ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ማውደሙን ጠቁሟል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
