የቀጣይ ቀናት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታ
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የትንበያ መረጃ እንደሚያመላክተው፤ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።
ኢንስቲትዩቱ አያይዞም በግንቦት የመጀመሪያው 10 ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም በጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ32 እስከ 39 ነጥብ 6 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚሆን ተመላክቷል።
በተያያዘ መረጃም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚገኙ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ፣ ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ኢንስቲትዩቱ አብራርቷል።
በተጠናቀረው የትንቢያ መረጃ በእነዚሁ ቀናት በጥቂት የደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ተገልጿል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
