EthiopiaNews

የቤተእስራኤላውያን ጥቃት

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚፈፀም የዘረኝነት ጥቃትን እንደሚያወግዙ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ወደ እስራኤል ለመግባት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ቤተ እስራኤላዊያንን ለማሰብ በተዘጋጀ አንድ የመታሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በቤተ እስራኤላዊው ይማኑ ቢንያም ላይ የተፈፀመው ጥቃትን አውግዘው ገዳዮቹ በፍ/ቤት እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ቤኒያሚን ኔታናያሁ በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚቃጣ ማናቸውንም ጥቃት እና መድልኦ እንደሚዋጉ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተ እስራኤላዊያንን ከመላው የእስራኤል ማህበረሰብ ጋር የማስተሳሰር ስር ውጤታማ መሆኑን ገልፀው ይሁን እንጂ አንዳንድ ያልተፈቱ ችግሮች እንዳሉ አንስተዋል። ዘገባው የኢየሩሳሌም ፖስት ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv