የብሔራዊ ባንክ የምንዛሪ ጨረታ ውጤት
በዛሬው የ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የብሔራዊ ባንክ የመጀመሪያ የምንዛሪ ጨረታ ውጤት ከጥቁር ገበያው ዋጋ ጋር ያለውን ልዩነት ማጥበብ የተቻለበት ነው ሲሉ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል ።
የብሔራዊ ባንክ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወዲህ የመጀመሪያው የሆነውን ልዩ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ ሲያደርግ 27 ባንኮች እንደተሳተፉበት ተነግሯል።
በዚህ ልዩ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 107.9 የኢትዮጵያ ብር ለአንድ የአሜሪካ ዶላር የቀረበ የአሸናፊዎች አማካይ ከፍተኛ ዋጋ መሆኑ ታውቋል።
ይህም ከ ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም ጀምሮ በዉጪ ምንዛሪ ተመን ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።