Ethiopia

የብጹዕነታቸው መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች መንግሥት ከሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር የተፈረደባቸው የሞት ፍርድ እንዲነሳላቸውና ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት መንገድ እንዲያመቻች ጠየቁ፡፡

ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ፓትርያርኩ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጠቀሜታው የሰው ልጆችን ሕይወት ለመጠበቅ መሆኑን በመጥቀስ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን ዜጎች ለመታደግ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሳዑዲ ባለሥልጣናት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ታሪክና ወዳጅነት አስበው ቅጣቱን እንዲያስቀሩ የጠየቁት ፓትርያርኩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም በማያውቁት ቋንቋ እንዲሁም ባልተረዱት የሕግ ሂደት ሞት የተፈረደባቸውን ወገኖች ስቃይ ተመልክተው የፍትሕ መዛባትን እንዲቃወሙና የንጹሐንን ነፍስ እንዲታደጉ ጠይቀዋል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv