EthiopiaNews

የትራምፕ ማፈግፈግ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ተማፅኖ ምክንያት በኢራን ላይ ዳግም ጥቃት የመሰንዘር ዕቅዱን ለጊዜው መሰረዛቸውን ገለፁ።

ፕሬዝዳንቱ ከዛሬ ጀምሮ በኢራን ላይ መካሄድ ሊጀምር የነበረው ጥቃት የተቋረጠው የቀጠናው ሀገራት ባቀረቡት ጥያቄ መሆኑን ጠቁመው አሁን ላይ ጠንካራ የሆነ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ በለጠፉት መልዕክት የኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያና የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ መሪዎች ባቀረቡት ጥያቄ ለጊዜው ጥቃቱ እንዲዘገይ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ኢራን የኒውክለር ጦር መሣሪያ መቼውም ቢሆን ሊኖራት አይገባም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ቴህራን አሁን ለዋሽንግተን የሚስማማ ስምምነት ላይ ትደርሳለች ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ኢራን የምታቀርበው የስምምነት ሃሳብ ተቀባይነት ከሌለው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደሚጠብቃት ማስጠንቀቃቸውን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/