የትግራይ ክልል ምክክር
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በአዲስ አበባ በማካሄድ አጀንዳዎችን ተረክቧል፡፡
ባለድርሻ አካላቱ 11 የሚሆኑ ዋና ዋና አጀንዳዎችን እና 51 የሚሆኑ ዝርዝር አጀንዳዎችን ማስረከባቸውን ሰምተናል፡፡
የሀገራዊ ምክክሩን የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ ስራ በትግራይ ክልል ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ ባለመፈጠሩ የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በአዲስ አበባ ቢያካሂድም በትግራይ ክልል መደረግ እንዳለበት ግን ከሚሽኑ እንደሚያምን ዋና ከሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በአጀንዳ ርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡
አሁን የቀረቡት አጀንዳዎች በአብዛኛው በሌሎች ክልሎች ከቀረቡት ጋር ተመሳሳይ እንደሆኑና በዋናው ጉባኤ ላይ ተነስተው ለውይይት እንደሚቀረቡም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ካሳለፍነው መጋቢት 23 እስከ ዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
