የነሐሴ ወር የነዳጅ ዋጋ
የነሐሴ ወር 2016 ዓም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ምንም አይነት ጭማሪ ሳይደረግበት ሐምሌ ወር በነበረበት የመሸጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግስት መውሰኑን ሰምተናል።
ከነዚህም ውስጥ ቤንዚን በነበረበት 82.60 በሊትር እንዲሁም ነጭ ናፍጣ በነበረበት 83.74 ብር በሊትር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗዋል፡፡
በመሆኑም የነዳጅ ማደያዎች ያልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ትእዛዝ መተላለፍን መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ የንግድ መዋቅሩ ተቆጣጣሪዎች በነዳጅ ስርጭትና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ የጋራ መግባባት ላይ ስለመደረሱ ተነግሯል።