InternationalNews

የአሜሪካ ቪዛና አፍሪካ

አሜሪካ በበርካታ የአፍሪካ ኤምባሲዎቿ ቪዛ መስጠትን ስታቆም የአዲስ አባባው ኤንባሲዋ ግን አገልግሎቱን ይቀጥላል ተብሏል።

አሶሼትድ ፕሬስ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ነገሩኝ እንዳለው አሜሪካ በአፍሪካ ካሉት 50 የሚደርሱ ኤንባሲዎችና ቆንስላዎች 20ው ብቻ የቪዛ ጉዳይን እንዲመለከቱና እንዲወስኑ ተደርጓል።

በዚህም ሂደት ቪዛ የሚሰጡ ኤንባሲዎችና ቆንስላዎች የሌሉባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች የአሜሪካ ቪዛን ለማግኘት በቅድሚያ ወደሚቀርባቸውም የአፍሪካ ሀገር ተጉዘው ማመልከት ይኖርባቸዋል።

ከአፍሪካ ቀንድ አዲስ አበባ፣ ጅቡቲ እና ናይሮቢ ብቻ የአሜሪካ ቪዛን ለማግኘት ማመልከት ይቻላል።

በዚህ ውሳኔ መሰረት በሰሜን አፍሪካ ያሉ የአሜሪካ ኤንባሲዎች በሙሉ ቪዛ ለአመልካቾች መስጠት አይችሉም ማለት ነው።

አሜሪካ ከአሁኑ ውሳኔ የደረሰችው የትራምፕ አስተዳደር አፍሪካዊያንን ስደተኞችን ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ባሉበት ለማገድ ባለው ውሳኔ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv