የአሜሪካ ኩባንያዎች ተሳትፎ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ለማሻሻልና ዘርፎችን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉት ስራዎች የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለ ምንም ስጋት በስፋት ኢንቨስት ለማድረግ ምቹና ተስማሚ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ ይሄንን የገለጹት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ጋር የአሜሪካ ባለሀብቶች በሀገሪቱ ባሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ ሊሳተፉ በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
አምባሳደሩ አክለውም የአሜሪካ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በስፋት በተለይም በዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በማዕድን፣ በጤና፣ በመሠረተ-ልማት፣ በፋይናንስ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን ይህንን ዕውን ለማድረግም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን በበኩላቸው በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለው የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ይሰራል ነው ያሉት፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews