EthiopiaNews

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በህወሐት አመራሮች ና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ክልከላ አደረገ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በህወሐት ከፍተኛ አመራሮች እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ክልከላ ማድረጉን አስታወቀ።

የቪዛ ገደቡ በህወሐት ከፍተኛ አመራሮች እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የተጣለው አመራሮቹ በኢትዮጵያ እና በቀጠናው ሰላም እና ደህንነት ላይ አደጋ በመደቀናቸው ነው ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በትግራይ ያለው ችግር በሰላም እንዳይፈታ እነዚሁ አመራሮች እንቅፋት መሆናቸውን ነው በመግለጫው የተጠቆመው።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በኢትዮጵያ እና በትግራይ ሰላም እንዲሰፍን ከኢትዮጵያ እና ከትግራይ ህዝብ ጎን ነን ብሏል።

መስሪያ ቤቱ የህውሃት አመራሮች ለኢትዮጵያ እና ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እንቅፋት ከሆኑ አመራሮቹን ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉንም አማራጮች እንደሚጠቀም ገልጿል።

ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ በመግለጫው የቪዛ ገደብ የተጣለባቸው የህወሃት አመራሮች ስም ዝርዝር ይፋ አላደረገም። መረጃው ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv