የአሜሪካ ጥቃት በኢራን
አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን የሚሳኤል ተቋማት ናቸው ያለቻቸውን ኢላማዎች መታሁ አለች።
አሜሪካ ድንገት ጥቃቱን የፈፀመችው ትላንትና ከኢራን ጋር አንዳች ስምምነት መደረሱን ስትገልፅ ቆይታ ነው። ይሄን ተከትሎም ሰላም ይሰፍናል በሚል ተስፋ የዓለም ነዳጅ ገበያም ቀንሶም ነበር።
አሁን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ እንደሚለው እርምጃው የተወሰደው እራስን ለመከላከልና የአሜሪካ ወታደሮችን ደህንነት ለማረጋገጥ ነው።
የማዕከላዊ ዕዙ ቃል አቀባይ ካፒቴን ቲም ሀውኪንስ ልክ እንደአሁኑ የአሜሪካ ወታደሮችን ደህንነት እያስጠበቅን ጐን ለጐን የተደረሰውን ተኩስ አቁም እናከብራለን ሲሉም ተደምጠዋል።
ኢራን እስካሁን ለአሜሪካ ጥቃት ምላሽ አልሰጠችም። የአሁኑ ጥቃትም በቀጣይ የሁለቱ አገራት ድርድር ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
