InternationalNews

የአሜሪካና ኢራን ግጭት

አሜሪካ እና ኢራን በትላንትናው ዕለት ተኩስ ከተለዋወጡ በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት አሁንም ተግባራዊነቱ መቀጠሉን ገለፁ፡፡

ለግጭቱ ሁለቱም ሀገራት አንዱ አንዱን ተጠያቂ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አሜሪካ በሶስት የጦር መርከቦቿ ላይ ኢራን የሚሳኤል፣ ድሮን እና ፈጣን ጀልባዎች ጥቃት መፈጸሟን ነው ያሳወቀችው፡፡

የኢራን ከፍተኛ የጦር አመራር በበኩላቸው አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ሲጓዙ በነበሩ የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሟን እንዲሁም በድንበር አከባቢዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ግጭቱ እንዲቀሰቀስ አድርጓል ብለዋል፡፡

ይህ የሁለቱ ሀገራት ግጭት የተቀሰቀሰው ደግሞ የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ መርምረው ጦርነቱን በዘላቂነት ማስቆም የሚያስችል ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጁ መሆናቸውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews