የአኮቦ ሚኒራልስ ምርት
መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገው አኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ ከጋምቤላ ክልል ወርቅ ማውጫው ባለፉት ሦስት ወራት 23 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረቱን አስታወቀ።
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ወርቅ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ፍቃድ ያገኘው ኩባንያው በመጋቢት ወር ብቻ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረቱን ባወጣው መረጃ ጠቅሷል።
በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ የተከሠተው የነዳጅ እጥረት ከተባባሰ የስራ መስተጓጎል ስጋት እንዳለበት የጠቀሰው ኩባንያው በዚህ ወቅት ምርቱን ለውጭ ገበያ እያቀረበ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
