EthiopiaNews

የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለአሚሶም

የአውሮፓ ህብረት በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ “አሚሶም ” የ75 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ መመደቡን አስታወቀ።

በአፍሪካ ህብረት የህብረቱ አምባሳደር ኒኖ ፔሬዝ ድጋፉ በሶማሊያ እና በቀጠናው ሀገራት ፀጥታን ለማረጋገጥ የሚካሄደውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ፣ የሰላም እና የፀጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴኦዬ ሕብረቱ ያደረገውን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደንቁ ተናግረዋል።

መረጃው ከአፍሪካ ህብረት የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv