የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይሄን ያስታወቁት ትናንት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው።
በተያዘው በጀት ዓመትም የመኖሪያ ቤት እጥረቱን በዘላቂነት ለመቅረፍ በመንግስት፣ በሪል እስቴት አልሚዎች፣ በግል ባለሀብቶች፣ በህብረት ሥራ ማኅበራትና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት በድምሩ 179 ሺህ 516 ቤቶች ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም መካከል በመንግስት በጀት እንዲገነቡ የታቀዱት የቤቶች ብዛት 50 ሺህ 305 ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት አማካይ የግንባታ አፈጻጸማቸው 40 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ በመዲናዋ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 496 ሺህ 971 ቤቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል፡፡
