የአፍሪካና አውሮፓ ስምምነት
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያትና የአውሮፓ ህብረት የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዩሮ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው የኢትዮጵያ-አውሮፓ ህብረት የቢዝነስ ፎረም መክፈቻ ላይ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያትና የአውሮፓ ህብረት የተፈረመው ስምምነቱ የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማሳለጥ የሚያግዝና በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደ ከፍተኛ ደረጃ የምጣኔ ሀብታዊ ትስስርና ንግድ ውይይት ያሉ መድረኮችን ጨምሮ የባለብዙ ወገን ተሳትፎን ያሳድጋል ሲባል የአውሮፓ ባለሀብቶችም በአፍሪካ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስና በተለያዩ ዘርፎች እሴት ለመጨመር ያግዛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
