InternationalNews

የኢራን ጦርነት

🔸አሜሪካ በኢራን የጀመረችውን ጦርነት በሁለትና ሦስት ሳምንታት እንደምታጠናቅቅ አስታወቀች።

🔸የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደሚሉት ኢራን ከአንዳች ስምምነት ለመድረስ ፈቃደኝነት እያሳየች በመሆኑ ጦርነቱ በጥቂት ሳምንታት የመጠናቀቅ ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡

🔸በሌላ በኩል ኢራን ስምምነት ደረሰችም ወይም ሌላ እኛ ኢራን ለረጅም ዓመታት ኒውክለር የመገንባት እቅም እንደማይኖራት ካረጋገጥን በዚያች አገር የምንቆይበት ምክንያት የለም ብለዋል ትራምፕ፡፡

🔸ትራምፕ ይህን ያሉት የኢራን ባለስልጣናት ጦርነቱ የሚቆመው ቴሄራን አስፈላጊ በመሰላት ጊዜ ነው እያሉ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

🔸የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን በበኩላቸው አገራቸው ከጠላት ወገን ውጊያ ለማቆም ዋስትና ከተሰጣት ጦርነቱን ለማቆም ዝግጁ ናት ማለታቸውን ሰምተናል፡፡

🔸በሌላ በኩል ፓኪስታንና ቻይና ጦርነቱ የሚቆምበትን ባለ አምስት ነጥብ የሰላም ሃሳብ ማቅረባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews