EthiopiaNews

የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች

🔸የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ማካሄድ ጀምሯል::

🔸የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በስምንት ወራት ውስጥ ከ6.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ንግድ ገቢ መገኘቱን ተናገሩ።

🔸የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዛሬ በመዲናዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተባበሩት አደባባይ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን እና በ3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን አስታወቀ።

🔸የጤና ሚኒስቴር ለ1.9 ሚሊየን ሰዎች የአይን ቆብ ቀዶ ጥገና ሕክምና እንደተደረገላቸው አስታወቀ።

🔸የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ማንኛውም ሰው ሎተሪን የሚመለከት ማስታወቂያ መስራት የሚችለው በሕግ አልያም አግባብ ባለው የመንግስት አካል የሎተሪን ሥራ ለማካሄድ የተሰጠ ፈቃድ ሲኖረው ብቻ መሆኑን ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews