EthiopiaNews

የኢቦላ ወረርሽኝ መስፋፋት

🔸የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጐ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ቀድሞ ከታሰበው በላይ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው አለ።

🔸በሽታው የተቀሰቀሰበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው አሁን በኢቦላ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የሚሞቱበት ፍጥነት ቀድሞ ከሚታወቀው በእጅጉ የባሰ ነው።

🔸የዲሞክራቲክ ኮንጐ ባለስልጣናት እንደሚሉት እስካሁን 136 ሰዎች በበሽታው ተይዘው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን 514 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ታመዋል።

🔸የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች የበሽታውን ዝርያ እያወቅን በመጣን ቁጥር ቫይረሱ በፍጥነት እንደሚሰራጭ ነው ያወቅነው ብለዋል።

🔸በለንደን የሚገኝ አንድ የምርምር ጣቢያ ደግሞ ታማሚዎች በቅጡ ስላልተለዩ እንጂ ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ ሊልቅ ይችላል ብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews