EthiopiaNews

የኢትዮ_ አፍሪኤግዚም ምክክር

ኢትዮጵያና አፍሪኤግዚም ባንክ ለወቅታዊው የዓለም ቀውስ ምላሽ መስጠት በሚቻልበትና የአፍሪካን የፋይናንስ አቅም ለማንቀሳቀስ የሚቻልባቸው ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውይይቱ አፍሪካ በኢኮኖሚ ራሷን ለመቻል የያዘቻቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮግራሞችና አህጉራዊ የንግድ ግንኙነት የሚሰፋበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

እንዲሁም በኢንዱስትሪ፣ የፋይናንስ መሰረተ ልማትና የፋይናንስ ዘርፍ ላይ መተባበር እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን አፍሪኤግዚም ባንክ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር በቅርበት የሚሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN