የኢትዮጵያ ልኡክ በአሜሪካ
በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከፍተኛ የልዑካን ቡድኑ ከትናንት ጀምሮ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ መካሄድ በጀመረውና እስከ መጪው አርብ ድረስ መካሄዱን በሚቀጥለው የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የፀደይ ወራት አመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ስለመሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝን ጨምሮ ሌሎች አባላትን ያካተተው ልዑኩ ከሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት በተጨማሪ የተለያዩ የሁለትዮሽና ከበርካታ የባለብዙ ወገን ድርጅቶችና ተቋማት ጋር ተከታታይ ውይይቶች ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
