EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ባለፉት 4 አመት ተኩል ውስጥ ሃብቱ ወደ 8.2 ትሪሊዮን ብር ደረሰ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ባለፉት 4 አመት ተኩል ውስጥ የኩባንያው ሃብት ወደ 8.2 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ተናገሩ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይሄን ያሉት ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ ላይ ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ባለፉት 4 አመት ተኩል ውስጥ ኩባንያው ስድስት ነጥብ ዘጠኝ ትሪሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን እና 715 ቢሊዮን ብር ግብር መክፈሉን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በእነዚሁ አመታት ውስጥ አምሳ ሁለት ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን እና 3.9 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳቡም በመድረኩ ተነግሯል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv