የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድርድር
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ የሚያደርጉት ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ለሁለተኛ ዙር በቱርክ አሸማጋይነት በተናጠል ከትላንት ጀምሮ በአንካራ እየመከሩ እንደሆነ የቱርኩ የዜና ወኪል አናዱሉ ዘግቧል።
ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ድረስ በተደራዳሪዎቹም ሆነ አዳራዳሪዎች ስለድርድሩ የወጣ ዝርዝር መረጃ አላገኝንም።