EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከ438 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 422.5 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 16.1 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 438.6 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 26 ተጠርጣሪዎች እና 13 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ መረጃው ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews