EthiopiaNews

የኢንቨስትመንት ፈቃድ

🔸የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአራተኛው የኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ ፎረም ላይ የ10 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት የተፈራረመው የቻይናው ሚንግ ያንግ ግሩፕ በሚቀጥሉት ሳምንታት የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደሚሰጠው አስታወቀ።

🔸ከሚሽኑ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ኩባንያው በፍጥነት ወደስራ መሰማራት በሚችልበት ላይ መምከሩን ገልጿል።

🔸ኮሚሽኑ ለኩባንያው አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚደረግለት ገልጿል።

🔸ሚንግ ያንግ ግሩፕ በታዳሽ ኃይል፣ በሃይድሮጅንና በግሪን አሞኒያ ምርት ዘርፎች የሚሰማራ ሲሆን በአራተኛው የኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ ፎረም ከተፈረሙትና በድምሩ 13.1 ቢሊዮን ዶላር ካስመዘገቡት ሰባት ስምምነቶች መካከል ከፍተኛውን የ10 ቢሊዮን ዶላር ድርሻ የያዘ መሆኑ ይታወሳል።

👉መረጃው ከኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews