EthiopiaNews

የኤምባሲው ማሳሰቢያ

🔸በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት መቀመጫቸውን በሊባኖስ አድርገው ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በመተባበር መደበኛ ባልሆነ መንገድ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ ሊባኖስ እንዲገቡ የሚያደርጉ ሰዎች ከአሳሳች ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

🔸ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ይሄን ማሳሰቢያውን የሰጠው በርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሊባኖስ እየገቡ መሆኑን ባስተወቀበት መግለጫ ነው።

🔸ኢትዮጵያውያን ዜጎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሊባኖስ እየገቡ በመሆኑ ሳቢያ መብቶቻቸውን እና ጥቆሞቻቸውን ማስከበር ፈተና እየሆነ ነው ተብሏል።

🔸ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለስራ ወደ ሊባኖስ መምጣት የሚችለው በህጋዊ ኤጀንሲዎች አማካኝነት ብቻ መሆኑን ገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews