InternationalNews

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን አሳወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ስልጣናቸውንና የሌበር ፓርቲ መሪነታቸውን መልቀቃቸውን ሲያሳውቁ ባደረጉት ንግግር ስልጣን ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ያሳለፉት ውሳኔ ሁሉ ሀገራቸውን በማስቀደም መሆኑን ገልፀዋል።

ስታርመር ሌበር ፓርቲያቸው ቀጣዩን መሪ እስኪመርጥ ድረስ በስልጣን ላይ እደሚቆዩ አሳውቀዋል።

ኬይር ስታርመር ስልጣን መልቀቃቸውን ከማሳታቃቸው ቀደም ብሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ጠቁመው ለውድቀታቸውም ስደትና ኢነርጂ ላይ የወሰዷቸው እርምጃዎችን ጠቅሰዋል። ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው።

የቀድሞው የፓርላማ አባል አንዲ በርንሀም የሌበር ፓርቲ መሪ ይሆናሉ ተብሎ በመጠበቁ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትርነት በቀጣይ እንደሚረከቡ ተጠቁሟል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv