የኮሚሽነሩ ሥርዓተ ቀብር
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
በሥርዓተ ቀብሩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮችና ባለሙያዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከአባታቸው አቶ አስፋው አብዲ ብሩና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙሉ ዳዲ በ1934 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ እንደተወለዱ የህይወት ታሪክ ማህደራቸው ያመለክታል፡፡
ኮሚሽነሩ ከየካቲት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews