የውጭ ንግድ ገቢ
በተያዘው የ2018 ግማሽ አመት ከውጭ ንግድ ታክስ ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ 51 በመቶ ብቻ መሰብሰቡን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
ሚኒስቴሩ ይሄንን ያስታወቀው የ2018 ግማሽ አመት አፈፃፀምን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት ላይ ሲሆን ከዘርፉ ለማግኘት ከታቀደው 578 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ማግኘት የተቻለው 295 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡
ገቢው ለማግኘት ከታቀደው አንጻር አነስተኛ ቢሆንም ነገር ግን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ123 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወይም የ72 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ተጠቁሟል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
