የውጭ ዕዳ ክፍያ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ከገቢዋ 26.3 በመቶውን ለውጭ ዕዳ ክፍያ እንደምታውል አስታወቀ።
ባንኩ ይሄን ያለው የፈረንጆቹ 2026 አመት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትንበያ አስመልክቶ ባወጣው አዲስ ዝርዝር ሪፖርቱ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2024 /25 በጀት አመት ካስገባችው ገቢ 26.3 በመቶውን ለውጭ ዕዳ ክፍያ እንዳዋለች በባንኩ ሪፖርት ተገልጿል።
ባንኩ አጠቃላይ የኢትዮጵያ እዳ ከሀገራዊ ጥቅል ምርት ውስጥ 42.8 በመቶ እንደሚሆን ገልፆ የሀገሪቱ የውጭ ዕዳ በፈረንጆቹ 2025 አመት ከተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ በ220 በመቶ እንደሚበልጥ ገልጿል።
ባንኩ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፈረንጆቹ 2025 /26 በሰባት ነጥብ 8 በመቶ እንዲሁም በፈረንጆቹ 2026 /27 ደግሞ በስምንት ነጥብ 5 በመቶ እድገት ሊያስመዘግብ ይችላል ሲል ትንበያውን ይፋ አድርጓል።
መረጃው ከአፍሪካ ልማት ባንክ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
