የዕዳ ሽግሽግ ድርድር
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከቻይና ጋር የሚካሄደው የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ አሁን ላይ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን ተናገሩ።
በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑካን በቻይና መዲና ቤጂንግ ጉብኝት አድርጓል።
ልዑካን ቡድኑ ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ፣ ከቻይና ኢንዱስትሪያል እና ኮሜርሻል ባንክ እንዲሁም ከቻይና ልማት ባንክ አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስትሩ የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ አሁን ላይ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰ መሆኑን ገልፀው ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ለመንግሥት ሰፊ የፋይናንስ ዕድል በመፍጠር ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በመሠረተ ልማት ፋይናንስና በሰፊ የኢኮኖሚ አጋርነት ዙሪያ ያላቸውን የቆየ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተገልጿል።
በተጨማሪም ሚኒስትሩ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ያለውን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት በመጥቀስ የቻይና ባንኮች የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
