EthiopiaNews

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በኢትዮጵያ ሊከስት ይችላል ተባለ

ኬንያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መከሰቱን የተናገረው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወረርሽኙ ለሀገራችንም ስጋት መደቀኑን በመግለፅ እንደሀገር ያለውን ዝግጁነት ገምግሞ ክፍተቶችን መለየቱን አስታውቋል።

በተለዩት ክፍተቶች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከል እና መቆጣጠር ዝግጁነት የማጠናከር ስራ እንደሚከናወን ኢኒስቲቲዩቱ ተናግሯል።