የጋምቤላ የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ
በጋምቤላ ክልል ከሀምሌ 22 እስከ ሀምሌ 28/2016 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ይህንኑ ተከትሎም በአጠቃላይ 495 የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች የለዩዋቸውን አጀንዳዎች የምክክሩ ባለድርሻ አካላት አደራጅተው ለኮሚሽኑ ማስረከባቸው ነው የተገለጸው፡፡ ከዚህ ባሻገር 115 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ማህበራት፣ 53 የመንግስት ተቋማትና 30 የፖለቲካ ፖርቲ ተወካዮች እንዲሁም 135 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳታፊዎች ሆነውበታል ተብሏል፡፡