EthiopiaNews

የጨረቃ ጉዞ

አርቴሚስ ሰከንድ በሚል ስያሜ ወደ ጨረቃ የተላኩት ጠፈርተኞች ተልዕኳቸውን አሳክተው ወደ ምድር እየተመለሱ ነው።

ተመራማሪዎቹ በጨረቃ ገፅ ላይ ባያርፉም ዙሪያዋን በመዞርና ከጨረቃ ጀርባ ድረስ በመጓዝ የሰው ልጅን ከፍተኛ የህዋ ጉዞ ርቀት ክብረወሰን ሰብረዋል።

ተልዕኮውን ይዛ የመጠቀችው ኦርዮን መንኮራኩር አዛዥ ሬይድ ዋይስማን እንዳሉት ቡድኑ የሰው ልጅ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀውን የጨረቃ ትዕይንት ለመመልከት ታድሏል።

ቡድኑ ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽን የተመለከተ ሲሆን የመንኮራኩሯ አብራሪ ቪክቶር ግሉቨር በጨረቃ ዙሪያ ያየነውን ትዕይንት የትኛውም ቋንቋ አይገልፀውም ብሏል።
አሜሪካ አሁን ከ50 ዓመታት በኋላ ያካሄደችው የጨረቃ ጉዞ ከቻይና ጋር የጀመረችው አዲስ የህዋ ሳይንስ ፉክክር ማሳያ ነው ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN