EthiopiaNews

የፀደቀው አዲስ ደንብ

🔸በኦሮሚያ ክልል ሕገ-ወጥ የመኖሪያ ቤቶችን ወደ ሕጋዊ መስመር የሚያስገባ አዲስ ደንብ መጽደቁን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

🔸የከተሞችን ፕላን ለማስጠበቅና ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ አልሟል የተባለው ይሀው አዲሱ ደንብ ከ2005 ዓ.ም እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተገነቡ ሕገ-ወጥ ቤቶችን ብቻ የሚመለከት መሆኑን የክልሉ መሬት ቢሮ ኃላፊ መሰረት አሰፋ ገልጸዋል፡፡

🔸በአዋጁ መሰረት በአንድ ከተማ ውስጥ ከአንድ ሕገ-ወጥ ግንባታ በላይ የሌለው ሰው መሆን እንደሚገባና የሚሰጠው የቦታ ስፋት የከተማውን ዝቅተኛ መመዘኛ መስፈርት መሠረት ያደረገ ይሆናል ያሉት ሃላፊዋ ሸገር፣ አዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች ዘመናዊ የካዳስተርና የዲጂታል የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን ቀድመው በመተግበራቸው ይህ ደንብ በእነዚህ ከተሞች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም ነው ያሉት።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews