InternationalNews

የፑቲን ጉብኝት በቤጂንግ

🔸የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይና ጋር ያለን ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ የላቀ ነው አሉ።

🔸የሩሲያው መሪ እንደሚሉት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

🔸ቻይና የሩሲያ ነዳጅን በመሸመት ቀዳሚዋ አገር ስትሆን ማዕቀብ ከተጣለባት ሩሲያ ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላት።

🔸ሞስኮና ቤጂንግ ባላቸው ግንኙነት ከሩሲያ 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፍ የሚችል ቱቦ ለመዘርጋት በመነጋገር ላይ ናቸው።

🔸አሁን በቤጂንግ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ፑቲን የቤጂንግ ቆይታቸው ዋና አላማ የዚሁ የተፈጥሮ ጋር ፕሮጀክት እውን መሆን ዋነኛ ነው ተብሏል።

🔸በተያያዘ ዜና ፕሬዝዳንት ፑቲን በመጭው የፈረንጆቹ ኅዳር ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በግንባር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

🔸ሁለቱ መሪዎች በግንባር የሚገናኙት ቻይና በምታዘጋጀው የእስያ ፓስፊክ አገራት ጉባኤ ላይ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews