የፓትርያርኩ መልዕክት
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ልሂቃን የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ እንዲያደምጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፓትርያርኩ ይሄንን ጥሪ ያቀረቡት የ2018 ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ መጀመሩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን ተልእኳችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ አሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት አይኖርም ነበር ብለዋል።
ይሁንና አሁንም ሕዝቡን ወደ አንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም ማምጣት የጉባኤያችን ዓቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጨምረውም ሀገሪቱን በኃላፊነት ተረክበው የሚመሩ እንዲሁም አማራጭ ሀሳብ አለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ልኂቃን የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ እንዲያደምጡም መልእክት አስተላልፈዋል።
ፓትሪያርኩ ሁሉንም ችግሮቻችን በሰላምና በሰላም ብቻ ለመፍታት እንድንተባበር ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
