EthiopiaNews

ጅቡቲ የደረሱት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች

143 ሺ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ የጫኑ 3 መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸው ተነገረ ።

በጅቡቲ ወደብ ሦስት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች መድረሳቸው የተሰማ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ ለተከሰተው የነዳጅ እጥረት መጠነኛ እፎይታ ሊሰጥ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።

ከመጋቢት 19 እስከ 23 ባሉት ጊዜያት ዉስጥ በጅቡቲ የደረሱት እነዚህ 3 መርከቦች በአጠቃላይ 143,000 ሜትሪክ ቶን የሚመዝን ናፍጣና የአውሮፕላን ነዳጅ የጫኑ መሆናቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

በኢራን ጦርነት ሳቢያ በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ማቅረብ እንዳልተቻለ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ካሳሁን ጎፌ መናገራቸው ይታወሳ

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN